Welcome to Souq Ecommerce Store !

ስለ እኛ

Goranda Systems ታኅሣሥ 2007 ዓ.ም በጌታሁን አማረ አያሌው የተመሠረተ  የስልክ መተግበርያዎችን የሚያዘጋጅ ድርጅት ሲሆን ድርጅቱ ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ ነፃ መተግበርያዎን ሲያቀርብ ቆይቷል አሁንም እያቀረበ ይገኛል፡፡

ድርጅቱ በአብዛኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ሥርዓትና ትውፊት የጠበቁ የጸሎት መጻሕፍትን፣ መጽሐፍ ቅዱስን፣ መዝገበ ቃላትንና የተለያዩ የቤተ ክርስቲያኗን ድርሳናትን ለምዕመናን እያቀረበ ይገኛል፡፡ በአሁን ሰዓትም ተጨማሪ መተግበሪያዎችን በመስራት ላይ ይገኛል፡፡

ጎራንዳ ማለት የቦታ ስም ሲሆን ይህም ቦታ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ ውስጥ የምትገኝ ልዩ ቦታ ናት፡፡ የድርጅቱ ስምም በዚች ድንቅ ቦታ ስም የተሰየመው አዘጋጁ በዚች ቦታ የተወለደና ያደገ ከመሆኑም በተጨማሪ ለዛሬ ማንነቱ መሠረት የጣለችለት ቦታ በመሆኗ ለመታሰቢያነት እንዲሆን አስቦ ነው፡፡

ጎራንዳ ሲስተምስ በቀጣይ ለኢትዮጵያውን መሠረት የሆኑ ታላላቅ መተግበሪያዎች የሚያዘጋጅ ሲሆን እነዚህን መተግበርያዎች በመጠቀም እውቀትዎን ማዳበር፣ የቅዱሳን አባቶችን ታሪክ ማወቅ፣ የኢትዮጵያን ቅርስና ታሪክ መገንዘብ እንዲሁም ለሕይወትዎ ጠቃሚ የሆኑ ነገሮችን ማግኘት ይችላሉ፡፡

ሥራችንን ለመደገፍ የምትፈልጉ በኢሜይል አድራሻን ወይም በስልካችን ሊያገኙን ይችላሉ፡፡

ስልካችን፡+251901008562
ኢሜይላችን: gorandasystems@gmail.com

Dictionaries & Apparel:

Jewelry & Watches:

Health & Beauty: